ከ4.1 ብር በላይ በሆነ ወጪ በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ ዙሪያ የሚገኘው የተንዳሆ ግድብና መስኖ ፕሮጀክት በ1997 ዓ.ም ተጀምሮ በ2009 ዓ.ም የተጠናቀቀው የተንዳሆ ግድብና የመስኖ ፕሮጀክት የ72 ኪሎ ሜትር የዋና ቦይ ግንባታ እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ እና የሶስተኛ ደረጃ ቦዮች. 1.8 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ያለው የተንዳሆ ግድብ 60,000 ሄክታር መሬት ማልማት ይችላል።
አዳዲስ ዜናዎች
ኮርፖሬሽኑ ቢግ 5 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን እየተሳተፈ ይገኛል
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) በዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው ቢግ 5 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በኮንስትራክሽን ግብዓት ማኑፋክቸሪንግ ምርት እና በኮንስትራክሽን መስክ ያለውም አቅምና ምርት እያስተዋወቀ ሲሆን በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ገበያ ውስጥ በመግባት ተወዳዳሪነቱን ለማፋጠን እያከናወናቸው ያሉ ጥረቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ ኤግዚቢሽኑ ከህዳር 17-20ቀን 2017ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ነው፡፡
ኢሲሲ ጂ አይ ደብሊው ኃላ.የተ.የግ.ማህበር
ኢትዮጵያ ኮንስራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) በ20.3 ቢሊዮን ብር ካፒታል በ2008 ዓ.ም የተቋቋመ የመንግስት ልማት ድርጅት ሲሆን ዋና ዋና ተጨማሪ ያንብቡ
ኢሲሲ- ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
ኢሲሲ-ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ከራይዚንግ ሆንግፋ ጋር በመሆን በሽርክና ካቋቋማቸው የምርት ማምረቻ ማዕከላት አንዱ ነው፡፡ የዚህን ማዕከል 70 በመቶ ድርሻ ኢ.ኮ.ሥ.ኮ ሲወስድ ቀሪውን 30 በመቶ ደግሞ የቻይና እና የህንድ ባለሀብቶች ይወስዳሉ፡፡ ማዕከሉ በሥሩ ሁለት የሥራ ክፍሎች ያሉት ሲሆን አንደኛው አገልግሎቱ ያለቀ ጎማን በመፍጨት ለእግረኛ እና ለመሮጫ ትራክ የሚያገለግሉ ምርቶችን ያመርታል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የተሻለ የጥራት ደረጃ ያላቸውን ሆሎ ኮር የህንፃ ወለል እና ግድግዳዎችን የሚያመርት ክፍል ነው፡፡
ሆሎ ኮር (ባለ ቀዳዳ) የህንፃ ወለል እና ግድግዳዎች ከተገጣጣሚ ህንጻ አካላት የሚመደቡ ሲሆን የህንፃው መሠረትና ስላብ የሚጠበቅባቸውን ጭነት እና ሌሎች ሁኔታዎችን የመቋቋም አቅማቸውን ሳያጡ የህንፃውን ጥቅል ክብደት የሚቀንሱ ኮንክሪትን በመጠቀም የሚመረቱ የህንፃ ወይም ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች ናቸው፡፡ በተገጣጣሚ ምርቶቹ ላይ ያሉት ባዶ ቦታዎች ወይም ክፍተቶች የህንፃውን መዋቅራዊ ጥንካሬ የማይቀነሱ ከመሆናቸው ሌላ ቀላል ክብደት ያላቸው በመሆናቸው ወደ ግንባታ ስፍራ እና በመገጣጠም ወቅት ለማንቀሳቀስ ምቹ ናቸው፤ እስከ 35 በመቶ የኮንክሪት ወጪን ለመቆጠብ ያስችላሉ፡፡
በእነዚህ ግብዓቶች የሚገነባ ህንፃ ጥሩ የድምፅ ስርገት የመቋቋም አቅም አለው፡፡ እሳትን ከመቋቋም እንፃርም ውጤታማ ግብዓቶች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ የቤቱን የሙቀትና ቀዝቃዜ መጠን የማመጣጠን ችሎታ አላቸው፡፡ ህንፃውን በቀላሉ በማፍረስ ምርቶቹን ለሌላ አገልግሎት ማዋል ይቻላል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥን የመቋቋም ችሎታቸውም ከፍተኛ ነው፡፡
ሆሎ ኮር የጥራት ደረጃውን የጠበቀ መደበኛ አርማታን እና በአንድ ላይ የተገመዱ ቴንሽን ገመዶችን በመጠቀም እና ቅድመ ቴንሽን የተደረጉ የሚመጣባቸውን ክብደት መቋቋም የሚችሉ ተገጣጣሚ ምርቶችን ያለምንም ሞልድ በማምረቻ ማሽኑ ቫይብሬሽን ብቻ የሚያመረት የማምረቻ ማሽን ነው፡፡
የማምረቻ ክፍሉ በመጀመሪያው የማስተዋወቂያ ጊዜ በመደበኛ የማምረት ሂደት በሳምንት 576ሜ2 ግድግዳ እና 1,200 የወለል ስፋት ስላብ ማምረት የሚችል ሲሆን የገብያ ፍላጎቱን መሰረት በማድረግ እስከ አራት እጥፍ ማምረት የሚያስችል እቅም አለው፡፡ ኢ.ኮ.ሥ.ኮ የ70 በመቶ ባለድርሻ እንደመሆኑ ግብዓቱን በሚሰራቸው ፕሮጀክቶቹ በመጠቀም አጠቃላይ ለህንፃው የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ እና ጥቅል የግንባታ እሴቶች ላይ አውንታዊ እምርታ በማምጣት ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት በሚል መሪ ቃል የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ተወያዩ
የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች ከለውጡ ወዲህ ባለፋት ስድስት አመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ተጨማሪ ያንብቡ
Latest project
ዲማ - የራድ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
Transport sector / completed ____Date:Feb 9, 2023
ዲማ - 60 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የራድ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይገኛል። የውል ስምምነቱ በጥር 16 ቀን 2015 የተፈረመ ሲሆን የውል መጠኑ ብር 874,442,881 ነው። የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ ነው። ፕሮጀክቱ በዚህ አመት 2020 የተጠናቀቀ ሲሆን ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር ያገናኛል።