
እንኳን ደስ አላችሁ!
ቀን: Feb 15, 2025
ላለፉት ሁለት ዓመታት በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ግንባታው የዘገየው በኢ.ኮ.ሥ.ኮ እየተገነባ የነበረው የያቤሎ ከተማ ባይፓስ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ የክልሉ መንግስት ችግሩን መፍታቱን ተከትሎ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

ኮርፖሬሽኑ በዓለም አቀፉ የመስኖ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ እየተሳተፈ ነው
ቀን: Feb 12, 2025
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን "የመስኖና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ ጉባዔ እየተሳተፈ ነው፡፡
ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በጉባዔው የተለያዩ የዓለም ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡ ጎን ለጎንም የመስኖ ሥራዎችን የሚያሳይ አውደርዕይ ለእይታ ክፍት ተደርጓል።
በዚህ ጉባኤ እና አውደርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለመስኖ እና ለውሃ ሥራዎች የሚያገለግሉ የተለያዩ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የፕሮጀክት ኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ
ቀን: Jan 29, 2025
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮሥኮ) ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር ከ5.5 ቢሊዮን ብር በላይ የኮንትራት ዋጋ ያለው ፕሮጀክት ለመገንባት የኮንትራት
ቀን: Jan 29, 2025
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮሥኮ) ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር ከ5.5 ቢሊዮን ብር በላይ የኮንትራት ዋጋ ያለው ፕሮጀክት ለመገንባት የኮንትራት
ቀን: Jan 27, 2025
የኢትዮጵያ ኮንስራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ባለፉት ዓመታት በሰው ኃብት ልማት፣ በዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎች ተከላ፣ አዳዲስ ሲስተሞችን በማበልጸግ እና የጥራት ፍተሻ ላቦራቶሪዎችን በማቋቋም የግንባታ ጥራትን እና ተወዳዳሪነቱን ከማሳደጉም ባሻገር ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር ሽርክና በመመስረት የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በማምረት የራሱን የግብዓት ፍላጎት ከማሟላት አልፎ ለገበያ በማቅረብ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን እየተካ ይገኛል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ይችል ዘንድ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ልህቀት ማዕከልን ያቋቋመ ሲሆን በማዕከሉ ስር ደግሞ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን አንድ ቦታ ሆኖ ለመቆጣጠር የሚያስችል የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል አደራጅቷል፡፡ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል ዋና ዓላማ 16ቱን የፕሮጀክት ማናጅመንት የዕውቀት መስኮች ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት የፕሮጀክቶችን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እና የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥርዓቱን ዘመናዊ ማድረግ ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል በተለያዩ የሥራ ቡድኖች የተዋቀረ እና በራስ ዓቅም የለሙ የተለያዩ ሶፍትዌሮች ያሉት ሲሆን ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ዕለታዊ የሥራ አፈጻጸም መከታተያ ሲስተም ፣ የተሽከርካሪዎች ማኔጅመንት ሲስተም እና የተቀናጀ የሀብት አስተዳደር አመራር ስርዓት (ERP) ይገኙበታል፡፡ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል የተቋሙን የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ሁለንተናዊ የሥራ እንቅስቃሴ በአንድ ቦታ ላይ ሆኖ ለመቆጣጠር ከማስቻሉም በላይ ኮርፖሬሽኑ ያለውን የሰው ኃብት እና ሌሎች ሀብቶችን ከወረቀት ነጻ በሆነ የሥራ አመራር ሥርዓት እንዲመራ የሚያስችል ነው፡፡ ቀን: Jan 10, 2025
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ለተከታታይ ዓመታት ባካሄዳቸው የለውጥ ሥራዎች አማካኝነት ከተመዘገቡ ከፍተኛ ውጤቶች መካከል አንዱ በተቋሙ የኢንዱስትሪ ማናጅመንት ዘርፍ፣ በአውቶሞቲቭ እና ማሽነሪ ጥገና ማዕከል ሥር የተቋቋመው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጥገና መምሪያ ነው፡፡ የከባድ ተሸከርካሪ ጥገና መምሪያ በሦስት ቡድኖች የተዋቀረ ሲሆን እነሱም ከባድ ተሸከርካሪዎች ጥገና፣ ሞተር ጥገና እና የተሸከርካሪዎች የአካል መገጣጠምና ቀለም ቅብ ቡድኖች ናቸው፡፡ መምሪያው በቀን ለ24 ሰዓታት በሁለት ሽፍት የሚሰጣቸው የጥገና አይነቶች ሁለት ሲሆኑ እነሱም የተሽከርካሪ አካል እድሳት እና የተሽከርካሪ አካልና የመለወጥ ሥራዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የተሽከርካሪዎች ቀለም ቅብ ሥራ የሚከናወነው “ካር ቡዝ” በተሰኘ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ቀለም መቀቢያ ቴክኖሎጂ ሲሆን እስከ አሁን በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የጥገና ማዕከላት ውስጥ ብቸኛው የቴክኖሎጂ ተጠቀሚ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ነው፡፡ የተሽከርካሪ አካል መለወጥ ሥራን በተመለከተ መምሪያው አገልግሎት የማይሰጥን አውቶቡስ የአካል ለውጥ በማድረግ “ሳፋሪ ባስ” የተሰኘች ለቱሪስቶች አመቺ የሆነች ተሽከርካሪ ሰርቶ ለአገልግሎት ብቁ ያደረገ ሲሆን ልምዱን ለሌሎች መሰል ተቋማት ለማካፈል ዝግጁ እንደሆነ መምሪያው ገልጿል፡፡ መምሪያው ለውስጥ እና ለውጭ ደንበኞች የከባድ ተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አሁን ላይ የውጭ ደንበኞቹ ቁጥር 22 ደርሷል፡፡ ጥቂቶቹን ለመግለጽ ያህል መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የመንግስት የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይገኙበታል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የፕሮጀክት ኮንትራት ስምምነት ተፈራረመ
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች መቆጣጠሪያ ክፍል
የከባድ ተሽከርካሪዎች ጥገና